blob: 2824444008d6c8e01ce36e1ae7fce59fa21f2c49 [file] [log] [blame]
አንቀጽ፡፩፤ የሰው፡ልጅ፡ሁሉ፡ሲወለድ፡ነጻና፡በክብርና፡በመብትም፡እኩልነት፡ያለው፡ነው።፡የተፈጥሮ፡ማስተዋልና፡ሕሊና፡ስላለው፡አንዱ፡ሌላውን፡በወንድማማችነት፡መንፈስ፡መመልከት፡ይገባዋል።
አንቀጽ፡፪፤ እያንዳንዱ፡ሰው፡የዘር፡የቀለም፡የጾታ፡የቋንቋ፡የሃይማኖት፡የፖለቲካ፡ወይም፡የሌላ፡ዓይነት፡አስተሳሰብ፡የብሔራዊ፡ወይም፡የኀብረተሰብ፡ታሪክ፡የሀብት፡የትውልድ፡ወይም፡የሌላ፡ደረጃ፡ልዩነት፡ሳይኖሩ፡በዚሁ፡ውሳኔ፡የተዘረዘሩት፡መብቶችንና፡ነጻነቶች፡ሁሉ፡እንዲከበሩለት፡ይገባል። ከዚህም፡በተቀረ፡አንድ፡ሰው፡ከሚኖርበት፡አገር፡ወይም፡ግዛት፡የፖለቲካ፡የአገዛዝ፡ወይም፡የኢንተርናሽናል፡አቋም፡የተነሳ፡አገሩ፡ነጻም፡ሆነ፡በሞግዚትነት፡አስተዳደር፡ወይም፡እራሱን፡ችሎ፡የማይተዳደር፡አገር፡ተወላጅ፡ቢሆንም፡በማንኛውም፡ዓይነት፡ገደብ፡ያለው፡አገዛዝ፡ሥር፡ቢሆንም፡ልዩነት፡አይፈጸምበትም።